am_tn/sng/08/02.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ወጣቷ ሴት ለሰውየው መናገሯን ትቀጥላለች።

እየመራሁህ ወደ እናቴ ቤት ባመጣሁህ

ሰውየው ወንድሟ ቢሆን ኖሮ ወደ ቤተሰቧ ቤት ማምጣት ትችል ነበር። ይህ በዚያ ባህል የተለመደና አሁንም በአንዳንዶች ዘንድ ልማድ የሆነ ነው።

ያስተማረችኝ እርሷ

የግብረ ሥጋ ግንኙነት እንዴት እንደሚፈጸም ያስተማረቻት

እንድትጠጣው ልዩ ከሆነው ወይን፣ ከሮማኔም ጭማቂ ጥቂት በሰጠሁህ

ሴቲቱ ራሷን እንደምትሰጠውና ከእርሱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት እንደምትፈጽም ለመናገር እነዚህን ምስሎች ትጠቀማለች።

የተቀመመ ወይን

“ወይን ከቅመማ ቅመም ጋር” ወይም “ቅመማ ቅመም ያለበት ወይን”። ይህ በግብረ ሥጋ ግንኙነት መስከርን ይወክላል።

ቀኝ እጁ … ያቅፈኛል

ይህንን በመኃልይ 2፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ግራ እጅ …ቀኝ እጅ

“ግራ ክንድ” … ቀኝ ክንድ”

ያቅፈኛል

“ይይዘኛል”