am_tn/sng/07/13.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሴቲቱ ለሰውዬው መናገሯን ትቀጥላለች።

ለመድኃኒት ቅመማ የሚያገለግሉ እፅዋት

ይህ ጠንካራ ነገር ግን አስደሳች ሽታ የሚለቁ እፅዋት ስም ነው። ሽታው በመጠኑ አስካሪና አነቃቂ ስለሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፍላጎትን ያነሣሣል።

መዓዛቸውን ሰጡ

“ሽታቸውን ለቀቁ” ወይም “በጣም ጥሩ ሽታ አላቸው”

በበሩ ላይ

በሮቹ የቤታቸው ነው። አ.ት፡ “ከቤታችን መግቢያ በላይ” ወይም “በቤታችን በሮች”

አዲስና የበሰሉ፣ ከሁሉም ዓይነት የተመረጡ ፍሬዎች

“ምርጥ የሆኑ የተለያየ ዓይነት ፍሬ፣ ከበሰለውና ከአዲሱ ፍሬ”

ለአንተ ተቀምጦልሃል

“ልሰጥህ እንድችል ተቀምጦልሃል”

ወዳጄ

ይህ ሐረግ ሴቲቱ የምትወደውን ሰውዬ ያመለክታል። በአንዳንድ ቋንቋዎች ሴቲቱ፣ “የእኔ አፍቃሪ” ብትለው በይበልጥ የተለመደ ሊሆን ይችላል። ይህንን በመኃልይ 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእኔ ውድ” ወይም “የእኔ አፍቃሪ”።