am_tn/sng/07/10.md

1.7 KiB

እኔ የወዳጄ ነኝ

ተመሳሳዩን ሐረግ በመኃልይ 6፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

የወዳጄ

ይህ ሐረግ ሴቲቱ የምትወደውን ሰውዬ ያመለክታል። በአንዳንድ ቋንቋዎች ሴቲቱ፣ “የእኔ አፍቃሪ” ብትለው በይበልጥ የተለመደ ሊሆን ይችላል። ይህንን በመኃልይ 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእኔ ውድ” ወይም “የእኔ አፍቃሪ”።

እኔን ይመኘኛል

“ከእኔ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለማድረግ ይፈልጋል” ወይም “ይፈልገኛል”

ሌሊቱን በመንደሮቹ ውስጥ እናሳልፍ

እዚህ ጋ ያሉት ቃላት “መንደሮች” እና “ሌሊቱን ያሳልፋል” ተብለው ቢተረጎሙም እንኳን በመኃልይ 1፡13-14 በአንድነት እንደ “ሌሊቱን ያሳልፋል” እና “የሄና አበቦች” ተብለዋል፣ እንዲሁም በዚህና በዚያ ያለው ዐውድ የሚያመለክተው የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸምን ነው። የተከፈተው የቃል በቃል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም፣ ተከታዩ ዘይቤአዊ አነጋገር ሰውየውና ሴቲቱ በመንደር ውስጥ ማደራቸውን፣ ማልደው መነሣታቸውንና ወደ ወይኑ ቦታ መሄዳቸውን ስለሚያመለክት እንዲህ ያለውን ንባብ ይመርጣል። “የሄና ተክሎች” እና “መንደሮች” የሚሉት ቃላት ድምፃቸው ተመሳሳይ ነው።