am_tn/sng/07/07.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሰውየው ከሴቲቱ ጋር ማድረግ የሚፈልገውን ይገልጻል።

ቁመናሽ እንደ የቴምር ዘንባባ ዛፍ ዘለግ ያለ ነው

“አቋቋምሽ እንደ ዘንባባ ዛፍ ነው”። የቴምር የዘንባባ ዛፍች ረጃጅምና ቀጥ ያሉ፣ ቅርንጫፎቻቸው አናቱ ላይ ብቻ የሚገኙና ፍሬአቸውን ከሥራቸው የሚያደርጉ ናቸው።

የቴምር ዘንባባ ዛፍ

እጅብ ብለው የሚያድጉ ጣፋጭ፣ ቡናማና ሙጫነት ያላቸውን ፍሬዎች የሚሰጥ ረጅምና ቀጥ ያለ ዛፍ

ጡቶችሽ የፍሬውን ዘለላ ይመስላሉ

ቴምር ለስላሳና ክብ ሆኖ በዘንባባ ዛፍ አናት ላይ ከቅርንጫፎቹ ሥር በሚንጠለጠሉ ረጃጅም ዘለላዎች ይገኛል። የሴቲቱ ጡቶችም ለስላሳ፣ ክብና ከክንዶቿ ዝቅ ያሉ ናቸው።

አልኩኝ

“አሰብኩኝ” ወይም “ለራሴ ተናገርኩ”። ሰውየው ይህንን የተናገረው በዝምታ ውስጥ ነው።

በቅርንጫፎቹ … ለመውጣት እፈልጋለሁ

ሰውየው ሴቲቱን ለማቀፍ ይፈልጋል።

ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ ይሁኑ

ሰውየው ጡቶቿን ለመንካት ይፈልጋል። የወይን ዘለላዎች ክብና ለስላሳዎች ናቸው።

የአፍንጫሽ መዓዛ እንደ እንኮይ ይሁን

“አፍንጫ” የሚለው ቃል ከአፍንጫ ለሚወጣው ትንፋሽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ከአፍንጫሽ የሚወጣው ትንፋሽ ሽታው እንደ እንኮይ ይጣፍጥ”

እንኮይ

የሚጣፍጥ ቢጫ ፍሬ