am_tn/sng/07/03.md

2.6 KiB

X

የወጣት ሴቷ አፍቃሪ የሚወዳትን እርሷን መግለጹን ይቀጥላል።

ሁለት ጡቶች

“ሁለት” የሚለው ቃል የማያስፈልግና ያለ ቦታው የተቀመጠ መስሎ ከታየህ ልትሰርዘው ትችላለህ። ይህንን በመኃልይ 4፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

እንደ ሁለት የአጋዘን ግልገሎች፣ መንታ የሜዳ ፍየል

ሰውየው ምናልባት የሴቲቱ ጡቶች እኩል፣ ለስላሳና ትንሽ መሆናቸውን ያመለክታል። ይህንን በመኃልይ 4፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

መንትዮች

ከአንዲት እናት በአንድ ጊዜ የተወለዱ ልጆች። ይህንን በመኃልይ 4፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

የሜዳ ፍየል

አጋዘን የሚመስልና በፍጥነት የሚንቀሳቀስ እንስሳ። በመኃልይ 2፡7 እንዳለው “የሜዳ ፍየሎች” የሚለውን በነጠላ ቁጥር ተርጉመው።

አንገትሽ እንደ ዝሆን ጥርስ ግምብ ነው

ግምብ ረጅምና ቀጥ ያለ ነው። የዝሆን ጥርስ ነጭ ነው። የሴቲቱ አንገት ረጅምና ቀጥ ያለ ነው፣ ቆዳዋም ብሩህ ቀለም አለው።

የዝሆን ጥርስ ግምብ

“ሰዎች በዝሆን ጥርስ ያስጌጡት ግምብ”

የዝሆን ጥርስ

አጥንት የሚመስል የእንስሳው ነጭ ጥርስ ነው። ሰዎች የጥበብ ሥራዎችን ለመሥራትና አንዳንድ ነገሮችን ለማሳመር በዝሆን ጥርስ ይጠቀማሉ።

ዓይኖችሽ እንደ ሐሴቦን ኩሬዎች ናቸው

የሴቲቱ ዓይኖች የጠራ የኩሬ ውሃ እንደሚመስሉ ተነግሮላቸዋል። የኩሬ ውሃ የጠራና የፀሐይ ብርሃን ሲያርፍበት ስለሚያንጸባርቅ ሲመለከቱት ያስደስታል። የሴቲቱም ዓይኖች የጠሩና አብረቅራቂዎች ናቸው፣ ስለዚህ ሲታዩ ያስደስታሉ። ይህ በምስስሎሽነት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ዓይኖችሽ በሐሴቦን እንዳሉት ኩሬዎች የጠሩ ናቸው”

ሐሴቦን

ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅ ያለች ከተማ ስም ነው

ባት ረቢ

የከተማ ስም

አፍንጫሽ በሊባኖስ እንዳለ ግምብ ነው ግምብ ረጅምና ቀጥ ያለ ነው፣ የእርሷም አፍንጫ ረጅምና ቀጥ ያለ ነው።