am_tn/sng/07/02.md

2.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

የወጣት ሴቷ አፍቃሪ የሚወዳትን እርሷን መግለጹን ይቀጥላል።

እምብርትሽ እንደ ክብ ጎድጓዳ ሳህን ነው

ጎድጓዳ ሳህን ክብ ነው። የሴቲቱ እምብርት ክብ ነው።

እምብርት

ልጅ ከእናቱ ጋር የሚያያዝበት እትብት የነበረበት፣ በሆድ ላይ የሚገኝ ምልክት

የተደባለቀ ወይን እንደማይጎድልበት

ሰዎች በግብዣ ላይ ወይንን በውሃ ወይም በቅመም ለማዋሃድ ትላልቅ ጎድጓዳ ሳህኖችን ይጠቀማሉ። ወይን መጠጣት በውበት የመደሰት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። የተጋነነው አባባል በአዎንታዊነት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ሁሌም የተደባለቀ ወይን እንደ ያዘ” ወይም “ሁሌም በውበቱ ልደሰት ይሆን”።

ሆድሽ በውብ አበቦች እንደ ተከበበ የስንዴ ክምር ነው

እስራኤላውያን የስንዴ ክምርና ውብ አበቦች ሲያዩአቸው የሚያስደስቱ እንደሆኑ ያስቡ ነበር። ብዙ ስንዴ፣ ለመብላት የሚሆን ብዙ ምግብ የመኖሩ ምልክት ነበር። ስንዴን የሚወቁት ከፍ ባለና በደረቅ ስፍራ ሲሆን የተዋቡት አበቦች የሚያድጉት በዝቅተኛና እርጥበት ባለባቸው አካባቢዎች ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ምልክታዊ ድርጊት ሰዎች በአብዛኛው በአንድ ጊዜ ሊያዩት የማይችሉትን አስደሳች ዕይታ አጣምሮ ያቀርባል።

ሆድሽ እንደ ስንዴ ክምር ነው

ሰዎች ስንዴ የሚመስለውን የሰውነት የቆዳ ቀለም እጅግ የተዋበ ቀለም እንደሆነ ያስቡ ነበር፣ በክብ የተከመሩ የስንዴ ክምሮችም ያምሩ ነበር። አ.ት፡ “የሆድሽ ቀለም ያማረ ነው፣ እንደ ስንዴ ክምርም ክብ ነው”

የስንዴ ክምር

ይህ ሰዎች የማይጠቀሙበትን ገለባውን ካስወገዱለት በኋላ የስንዴ ምርት ክምር ነው።

በተዋቡ አበቦች የተከበበ

ዙሪያው በተዋቡ አበቦች”

የተዋቡ አበቦች

ብዙ ውሃ በሚገኝበት አካባቢ የሚያድጉ ጣፋጭ ሽታ ያላቸው አበቦች ናቸው። በመኃልይ 2፡1 እንዳለው በብዙ ቁጥር አድርገህ ተርጉመው።