am_tn/sng/07/01.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ:

በአንዳንድ ትርጉሞች ይህ 7፡2 ነው፣ የሰባተኛው ምዕራፍ ሁለተኛ ቁጥር

በነጠላ ጫማዎችሽ ውስጥ ሲታዩ እግሮችሽ ምንኛ ያምራሉ

ምናልባት ሴቲቱ እየደነሰች ነው (መኃልይ 6፡13) ። አ.ት፡ “በምትደንሽበት ጊዜ በነጠላ ጫማዎቹ ውስጥ እግሮችሽ እጅግ በጣም ያማሩ ናቸው”

የልዑል ሴት ልጅ

ሌላው አማራጭ ትርጉም ሊሆን የሚችለው “አንቺ ምስጉን ጠባይ ያለሽ” የሚለው ነው።

የዳሌዎችሽ መታጠፊያዎች ዕንቁዎችን ይመስላሉ

የሴቲቱ ዳሌዎች ቅርፃቸው ለተናጋሪው ብልህ ቅርፃ ቅርፅ ሠሪ የሠራውን ውብ የከበረ ድንጋይ ያስታውሰዋል። አ.ት፡ “የዳሌዎችሽ መታጠፊያዎች ብልህ ቀራፂ እንደሚሠራቸው የተዋቡ የዕንቁ መታጠፊያዎች የተዋቡ ናቸው”።

ዳሌዎችሽ

“ዳሌዎችሽ” የሚለው ቃል የሴቲቱን ሽንጥና ከጉልበትዋ በላይ ያለውን የዳሌዋን ክፍል ያመለክታል።

የብልህ ቀራጺ እጆች የሠሩት

እጆች የሰው ምሳሌዎች ናቸው። አ.ት፡ “የብልህ ቀራጺ ሥራ” ወይም “ብልህ ቀራጺ የሠራው አንዳች ነገር”