am_tn/sng/06/13.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

በአንዳንድ ትርጉሞች ይህ 7፡1፣ የሰባተኛው ምዕራፍ የመጀመሪያ ቁጥር ነው። የተከፈተ የቃል በቃል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ይህንን የሚገነዘበው ሴቲቱና ጓደኞቿ እርስ በእርሳቸው እንደሚነጋገሩ ነው። አንዳንድ ትርጉሞች ደግሞ ሰውየው ለሴቲቱ የሚናገረው እንደሆነ ይገነዘባሉ።

ተመለሽ … እንድናይሽ

ትርጓሜዎች ሊሆኑ የሚችሉት 1) ጓደኞቿ ሴቲቱን እያናገሯት ነው ወይም 2) ሰውየው ራሱን በብዙ ቁጥር እያመለከተ ነው።

ተመለሽ፣ ተመለሽ

“ወደ ኋላሽ ተመለሽ፣ ወደ ኋላሽ ተመለሽ”። ይህ የተደገመው አጽንዖት ለመስጠት ነው።

እንድናይሽ

አንዳንድ ትርጉሞች ብዙውን ቁጥር ሰውየው ስለ ራሱ የሚናገረውን እንደሚያመለከት ይረዳሉ። አ.ት፡ “እንዳይሽ”

አተኩሮ መመልከት

ለረጅም ጊዜ በጥሞና መመልከት

እንከን ዐልባዋን ሴት አተኩራችሁ የምትመለከቷት ለምንድነው … ሰራዊቶች

ትርጓሜዎች ሊሆኑ የሚችሉት 1) ሴቲቱ ራሷን እንደ ሌላ ሰው አድርጋ ለጓደኞቿ ትናገራለች ወይም 2) ሴቲቱ ለብዙ ወንዶች እንደምትናገር አድርጋ ለሰውየው ትናገራለች።

በሁለት ሰራዊት መሐል እንደምትጨፍር

“በሁለት ሰራዊት መሐል ስትጨፍር እንደነበረች”