am_tn/sng/06/11.md

1.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሰውየው ለራሱ መናገሩን ያበቃል። እጽዋት በቅለው እንደሆነ ማየቱ ምናልባት የሴቲቱን ገላ በማየት ለመደሰት መፈለጉን የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ይሆናል።

ጫካ

ይህንን በመኃልይ 4፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ቡቃያ

“አዳጊ ተክሎች” ወይም “አዲስ ቦቆልቶች”

እንቡጥ አውጥቷል

እንቡጣቸው ማደግ ጀምሯል። እንቡጦች ወደፊት ተከፍተው አበቦች የሚሆኑ ትናንሽ፤ ክብ የተክል ክፍሎች ናቸው።

በመፍካት ላይ ነበሩ

“አበቦቻቸው እየተከፈቱ ነበር”

በንጉስ ሰረገላ ላይ እየጋለብኩ እንዳለሁ ያህል በጣም ደስተኛ ነበርኩ

ሰውየው ምን ያህል ደስተኛ እንደሆነ ለመግለፅ ይህን ምስል ይጠቀማል።