am_tn/sng/06/10.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

የተከፈተው የቃል በቃል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ይህንን የሚረዳው ንግስቶቹና ቁባቶቹ ስለ ሴቲቱ እንደተናገሩት ይገነዘባል። ይሁን እንጂ፣ አንዳንድ ትርጉሞች የሚገነዘቡት እነዚህን የሰውየው ቃላት እንደሆኑ ነው።

አርማ … እንደ ንጋት የምትታይ ይህቺ ማን ናት?

ይህንን ጥያቄ የሚጠቀሙት ወጣቷ ሴት አስደናቂ መሆኗን እንደሚያስቡ ለመናገር ነው። አ.ት፡ “ይህች አስደናቂ ሴት ናት! ዓርማ … እንደ ንጋት ትታያለች!”

እንደ ንጋት የምትታይ

ንጋት ውብ ነው። ሴቲቱ ውብ ናት። አ.ት፡ “እንደ ንጋት ወጥታ የምትታይ”

ዐርማቸውን ይዘው እንደሚያስፈሩ ወታደሮች

የሴቲቱ ውበት ኃያል ከመሆኑ የተነሣ ሌሎች ሴቶች ወታደሮች የመጡባቸው ያህል አቅመ ቢስነት እንዲሰማቸው አድርጓቸዋል። ይህንን በመኃልይ 6፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።