am_tn/sng/06/08.md

1.8 KiB

60 ንግስቶች እና 80 ቁባቶች አሉ … ከቁጥር ያለፉ ወጣት ሴቶች

እነዚህ ቁጥሮች በጣም ብዙ፤ እጅግ ብዙ፤ ከመቆጠርም ያለፉ ናቸው። አ.ት፡ “60 ንግስቶች፣ 80 ቁባቶች … ማንም ሊቆጥራቸው የማይቻለው በርካታ ወጣት ሴቶች አሉ” ወይም “ ብዙ ንግስቶች፣ ከዚያም የሚበልጡ ቁባቶችና ማንም ሊቆጥራቸው የማይችል ብዙ ወጣት ሴቶች”

እርግቤ

እስራኤላውያን እርግቦችን አስደሳች ድምፅ ያላቸው ውብ ወፎች እንደሆኑ ያስቡ ነበር። ሰውየው የሴቲቱ ፊትና ድምፅ ያማረ እንደሆነ ያስባል። አንዲትን ሴት “እርግብ” ብሎ መጥራት ቅር የሚያሰኛት ከሆነ ዘይቤአዊውን አነጋገር ልትተወው ትችላለህ። ይህንን በመኃልይ 2፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

የእኔ እንከን ዐልባ

“የኔ ፍፁም”ወይም “የኔ ታማኝ” ወይም “የኔ የዋህ”። ይህንን በመኃልይ 5፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ለእናቷ ብቸኛ ሴት ልጅ የሆነች

ይህ ግነት ነው። አ.ት፡ “ለእናቷ ልዩ የሆነች ልጅ” ወይም “ከእናቷ ከተወለዱት ከሌሎች እህቶቿ የተለየች”

የወለደቻት ሴት

“እርሷን የወለደቻት ሴት”። ይህ ሐረግ እናቷን ያመለክታል።

ወጣት ሴቶች … ንግስቶች … ቁባቶች

በቁጥር 8 የተነገረላት ሴት ናት

የተባረክሽ ብለው ጠሯት

“ነገሮች ለርሷ በጣም የተሻሉ እንደሆኑላት ተናገሩ”