am_tn/sng/06/06.md

2.0 KiB

ጥርሶችሽ በቅርቡ የተሸለቱ የሴት በጎች መንጋ ይመስላሉ

በጎች ጸጉራቸው ከተሸለተ በኋላ ይታጠቡና ቆዳቸው በጣም ነጭ ሆኖ ይታያል። የሴቲቱ ጥርሶች ነጭ ናቸው። በመኃልይ 4፡2 ላይ “ጥርሶችሽ በቅርቡ የተሸለቱ የሴት በግ መንጋ ይመስላሉ” የሚለው እንዴት እንደተተረጎመ ተመልከት።

ከመታጠቢያው ስፍራ የሚመጡ

ሴቶቹ በጎች ከውሃው ውስጥ ወጥተው እየመጡ ነው። ይህንን በመኃልይ 4፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ሰዎች ካጠቡዋቸው በኋላ ከውሃው ውስጥ ወጥተው የሚመጡትን”

እያንዳንዱ መንታ አለው

በጎች አብዛኛውን ጊዜ በአንዴ ሁለት ግልገሎችን ይወልዳሉ። እነዚህ መንታዎች ብዙውን ጊዜ ይመሳሰላሉ። እያንዳንዱ የሴቲቱ ጥርስ ከአፏ በሌላኛው ጎን ካለው ጋር እኩል ነው። ይህንን በመኃልይ 4፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ከእነርሱ አንዱም አልጎደለም

እያንዳንዱ የሴቲቱ ጥርስ ከአፏ በሌላኛው ጎን ካለው ጋር እኩል ነው። ከጥርሶቿ አንድም የወለቀ የለም።

ሐዘንተኛ

የቅርብ ሰው የሞተበት። ይህንን በመኃልይ 4፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

እንደ ሮማን ክፋይ ናቸው

ሮማኖች ደማቅ ቀይ፣ ክብ እና ለስላሳ ናቸው። ሰውየው የሴቲቱ ጉንጮች ያማሩና እርሷም ጤነኛ መሆኗን እንደሚያሳዩ ያስባል። ይህንን በመኃልይ 4፡3ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ከአይነርግብሽ በስተጀርባ

ይህንን በመኃልይ 4፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።