am_tn/sng/06/04.md

980 B

አጠቃላይ መረጃ፡

የመጽሐፉ ክፍል አምስት እዚህ ጋ ይጀምራል

የኔ ፍቅር እንደ ቴርሳ ውብ፣ እንደ ኢየሩሳሌም ተወዳጅ

እነዚህ ከተሞች በውበታቸው የታወቁና በውስጣቸው ለመኖር የሚያስደስቱ ነበሩ። ሰውየው ሴቲቱ ውብ እንደሆነችና ከእርሷ ጋር መሆን እንደሚያስደስተው ያስባል።

የኔ ፍቅር

“አንቺ የምወድሽ”፣ ይህንን በመኃልይ 1፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ተወዳጅ

ይህንን በመኃልይ 1፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ዐርማቸውን ይዘው እንደሚያስፈሩ ወታደሮች

የሴቲቱ ውበት ኃያል ከመሆኑ የተነሣ ሰውየው ወታደሮች የመጡበት ያህል አቅመ ቢስነት እንዲሰማው አድርጎታል።