am_tn/sng/06/02.md

2.7 KiB

ወዳጄ ወደ አትክልት ቦታው ሄዷል

“የአትክልት ቦታ” የሚለው ቃል ሴቲቱን የሚገልፅ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። በመጨረሻም ሰውየው ከሴቲቱ ጋር በፍቅር ግንኙነት ሙሉ ደስታ ማግኘት ችሏል። የዚህን ዘይቤአዊ አነጋገር ማብራሪያ በመኃልይ 5፡1 ውስጥ ተመልከት።

ወዳጄ

ይህ ሐረግ ሴቲቱ የምትወደውን ሰውዬ ያመለክታል። በአንዳንድ ቋንቋዎች ሴቲቱ ሰውየውን “የኔ አፍቃሪ” ብትለው በይበልጥ የተለመደ ይሆን ይሆናል። ይህንን በመኃልይ 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእኔ ውድ” ወይም “የእኔ አፍቃሪ”።

የቅመማ ቅመም መደብ

ሰዎች ቅመማ ቅመም የሚያበቅሉባቸው የአትክልት ስፍራዎች ወይም የአትክልት ስፍራ ክፍል። ይህንን በመኃልይ 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

በአትክልት ስፍራ ለመሰማራትና የተዋቡ አበቦችን ለመሰብሰብ

እነዚህ ቃላት ሰውየው በሴቲቱ ገላ መደሰቱን የሚያሳዩ ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው።

መሰማራት

“ይመግባል” ወይም “ሳር ይበላል”። ሴቲቱ ሰውየውን በተዋቡት አበቦች መሐከል እፅዋትን እንደሚመገብ “ሚዳቋ ወይም የአጋዘን ግልገል” ቆጥራ ትናገራለች (መኃልይ 2፡17)። መሰማራት ምናልባት የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸምን የሚገልፅ ዘይቤአዊ አነጋገር ሊሆን ይችላል (መኃልይ 2፡1-2)። “ይመግባል”ን በመኃልይ 2፡16 እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

የተዋቡትን አበቦች ለመሰብሰብ

“የተዋቡ አበቦችን ለመልቀም”

የተዋቡ አበቦች

ብዙ ውሃ ባለበት ቦታ የሚበቅሉ ባለጣፋጭ ሽታ አበቦች። በመኃልይ 2፡1 እንዳለው “የተዋበ አበባ” የሚለውን በብዙ ቁጥር ተርጉመው።

እኔ የወዳጄ ነኝ፣ ወዳጄም የእኔ ነው

“ወዳጄ የእኔ ነው፣ እኔም የእርሱ ነኝ” የሚለውን ተመሳሳይ ሐረግ በመኃልይ 2፡16 እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

በተዋቡት አበቦች መሐከል በደስታ ይግጣል

ይህንን በመኃልይ 2፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።