am_tn/sng/04/15.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ሰውየው ሴቲቱን ማድነቁን ይቀጥላል።

አንቺ የአትክልት ቦታ ምንጭ ነሽ

“በአትክልት ቦታ ያለ ምንጭ ነሽ”። በአትክልት ቦታ የሚገኝ ምንጭ ሰዎች ለመጠጣት የሚወዱትን ጣፋጭና ንፁህ ውሃ ይሰጣል። ሰውየው በሴቲቱ አጠገብ በመሆኑ ይደሰታል።

ንፁህ ውሃ

ለመጠጥ ጥሩ የሆነ ውሃ

ከሊባኖስ የሚወርዱ ምንጮች

ሊባኖስ በዛፍ የተሸፈኑ ተራሮች ስላነበሯት ከሊባኖስ የሚወርዱት ምንጮች ንጹሕና ቀዝቃዛ ነበሩ።

የሰሜኑ ንፋስ ተነሥ፤ የደቡቡ ንፋስ ና ንፈስ

ሴቲቱ የሰሜኑ እና የደቡቡ ንፋስ ሰዎች እንደሆኑ አድርጋ ትናገራለች። አ.ት፡ “የሰሜኑ ንፋስና የደቡቡ ንፋስ መጥተው ቢነፍሱ እወዳለሁ”

የሰሜኑ ንፋስ ተነሥ

“የሰሜን ንፋስ መንፈስ ጀምር”

በአትክልት ቦታዬ ላይ ንፈስ

የአትክልት ስፍራው መልካም ሽታ ባላቸው ቅባቶች የተቀባውን የሴቲቱን ገላ የሚገልጽ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው (መኃልይ 4፡14) ።

መዓዛቸውን ይስጡ

“መልካም ሽታቸውን ይልቀቁ”

ወዳጄ … ምርጥ ፍራፍሬ

ሴቲቱ ሰውየው አብሯት እንዲተኛ እየጋበዘችው ነው።

ወዳጄ

ይህ ሐረግ ሴቲቱ የምትወደውን ሰውዬ ያመለክታል። በአንዳንድ ቋንቋዎች ሴቲቱ “የኔ አፍቃሪ” ብትለው በይበልጥ የተለመደ ይሆን ይሆናል። ይህንን በመኃልይ 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእኔ ውድ” ወይም “የእኔ አፍቃሪ”።

ምርጥ ፍሬ

“ግሩም ፍሬ”