am_tn/sng/04/12.md

3.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሰውየው ሴቲቱን ማድነቁን ቀጥሏል።

የኔ እህት

ይህ የፍቅር አነጋገር ነው። በመሠረቱ እነርሱ ወንድምና እህት አይደሉም። ይህንን በመኃልይ 4፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእኔ ውድ” ወይም “የእኔ ፍቅር”

ሙሽራዬ

ይህ የዕብራይስጡ ቃል ያገባችን ሴት ወይም አንድ ሰው ወንድ ልጁን ለመዳር ያዘጋጃትን ሴት ይወክላል። በቋንቋህ ውስጥ ባል ለሚስቱ ሊጠቀም የሚችለው ጨዋነት ያለው ቃል ካለና እስካሁን በዚህ መጽሐፍ ካልተጠቀምክበት እዚህ ጋ ልትጠቀምበት ትችላለህ። ካልሆነም ባል ለሚስቱ ሊጠቀምበት የሚችለውን ሌላ የጨዋነት ቃል መጠቀም ትችላለህ። ይህንን በመኃልይ 4፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

የተቆለፈበት የአትክልት ስፍራ ነው

“ማንም ሊገባበት የማይችል የአትክልት ስፍራ”። የአትክልት ስፍራው ለሴቲቱ፤ ቁልፉ ደግሞ ለድንግልናዋ ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው።

የታተመ ምንጭ

“መክደኛ ያለው ምንጭ”። ምንጩ ወይም የውሃው ጉድጓድ ሴቲቱን፤ ሽፋኑ ደግሞ ድንግልናዋን የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው።

ቅርንጫፎችሽ

ቅርንጫፎች ወይም የወንዝ መውረጃዎች የሴቲቱን የሰውነት ክፍል በጨዋ አነጋገር የሚገልጹ ናቸው። የእነዚህ ቃላት አጠቃቀም ቅር የሚያሰኝ ከሆነ የሰውን ሁለንተና መግለጽ በሚችል የተሻለ ምሳሌአዊ አነጋገር ተርጉመው።

ጫካ

ብዙ ዛፎች በአንድ ላይ የሚበቅሉበት ስፍራ

ከምርጥ ፍራፍሬዎች ጋር

“ምርጥ ከሆኑ የፍራፍሬ አይነቶች ጋር”

የናርዶስ ተክሎች

ሰዎች ቆዳቸውን ለማለስለስና መልካም መዓዛ እንዲኖራችው የሚጠቀሙበትን ዘይት የሚሰጥ ተክል። ይህንን በመኃልይ 1፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ሄና

ሰዎች እንደ ሽቱ የሚጠቀሟቸው ትናንሽ የበረሃ ዛፎች። ይህንን በመኃልይ 1፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

እርድ

ከአንድ ዓይነት አበባ መሐሉ ላይ ከሚገኝ ቢጫ የደረቀ ክፍል የሚገኝ ቅመም

ቀጋ

ሰዎች የቅባት ዘይት ለመስራት የሚጠቀሙበት መልካም መዓዛ ያለው ተክል

ቀረፋ

ሰዎች ለማብሰል ከሚጠቀሙበት ዛፍ ቅርፊት የሚገኝ ቅመም

ከርቤ

እንደተረጎምከው ተመልከት።

ሬት

ጣፋጭ ሽታ ያለው፣ ሰፊ ቅጠል ያለው የተክል ዓይነት

ምርጥ ቅመማ ቅመሞች ሁሉ

“ምርጥ የሆኑ ቅመሞች ሁሉ”