am_tn/sng/04/10.md

3.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሰውየው ለሴቲቱ መናገሩን ይቀጥላል።

ፍቅርሽ እንዴት ያማረ ነው

“ፍቅርሽ ግሩም ነው”

እህቴ

ይህ የፍቅር አነጋገር ነው። በመሠረቱ እነርሱ ወንድምና እህት አይደሉም። ይህንን በመኃልይ 4፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእኔ ውድ” ወይም “የእኔ ፍቅር”

ሙሽራዬ

ይህ የዕብራይስጡ ቃል ያገባችን ሴት ወይም አንድ ሰው ወንድ ልጁን ለመዳር ያዘጋጃትን ሴት ይወክላል። በቋንቋህ ውስጥ ባል ለሚስቱ ሊጠቀም የሚችለው ጨዋነት ያለው ቃል ካለና እስካሁን በዚህ መጽሐፍ ካልተጠቀምክበት እዚህ ጋ ልትጠቀምበት ትችላለህ። ካልሆነም ባል ለሚስቱ ሊጠቀምበት የሚችለውን ሌላ የጨዋነት ቃል መጠቀም ትችላለህ። ይህንን በመኃልይ 4፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ እጅጉን ይሻላል

“ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ እጅግ የተሻለ ነው”። ተመሳሳዩን ሐረግ በመኃልይ 1፡2 እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

የሽቶሽ መዓዛ ከየትኛውም ቅመም

ግሱ ምናልባት ቀደም ብሎ ካለው ሐረግ ወስዶ ይሆናል። አ.ት፡ “ከየትኛውም ቅመም ይልቅ የሽቱሽ መዓዛ እጅግ የተሻለ ነው”

መዓዛ …ሽቱ

እነዚህን ቃላት በመኃልይ 1፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።

ቅመም

መልካም ሽታ ወይም ጣዕም ያላቸው የደረቁ እፅዋት ወይም ዘሮች

ከንፈሮችሽ … ማር ያንጠባጥባሉ

ማር ትርጓሜዎች ሊሆኑ ለሚችሉ ለሚከተሉት 1) የሴቲቱን የአሳሳም ጣፋጭ ጣዕም ወይም 2) የሴቲቱን ቃላት ለማመልከት የዋለ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው።

ከምላስሽ በታች ወተትና ማር አለ

“ወተትና ማር” በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተለመደ ሐረግ ስለሆነ ቃል በቃል መተርጎም አለብህ። ትርጉሞች ሊሆኑ የሚችሉት ማር የሚለው ዘይቤአዊ አነጋገር 1) የሴቲቱን የአሳሳም ጣፋጭ ጣዕም 2) የሴቲቱን ቃላት ሊሆን ይችላል። ወተት የምቾት፤ ሰዎች ሕይወትን ለማጣጣም የሚኖሯቸውን በርካታ ነገሮች የሚገልፅ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። ሴቲቱ ሰውየውን ስትስመው፣ እርሱ ሕይወትን ያጣጥማል።

የልብስሽ መዓዛ እንደ ሊባኖስ ሽታ ነው

“የልብስሽ ሽታ እንደ ሊባኖስ ሽታ ነው”። በሊባኖስ ብዙ የጥድ ዛፎች ይበቅሉ ነበር። የጥድ ዛፎች በጣም ጥሩ ሽታ አላቸው፤ በመሆኑም፣ሊባኖስ ንጹሕና ጣፋጭ ሽታ ሳይኖራት አልቀረችም።