am_tn/sng/04/09.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሰውየው ለሴቲቱ መናገሩን ይቀጥላል።

ልቤን ሰርቀሽዋል

የዚህ ፈሊጣዊ አነጋገር ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉት 1) “አሁን ልቤ ሙሉ በሙሉ ያንቺ ነው” ወይም 2) “ካንቺ ጋር የግብረ ሥጋ ለመፈጸም አጥብቄ እፈልጋለው” ናቸው።

የኔ እህት

ይህ የፍቅር አነጋገር ነው። በመሠረቱ እነርሱ ወንድምና እህት አይደሉም። አ.ት፡ “የእኔ ውድ” ወይም “የእኔ ፍቅር”

ሙሽራዬ

ይህ የዕብራይስጡ ቃል ያገባችን ሴት ወይም አንድ ሰው ወንድ ልጁን ለመዳር ያዘጋጃትን ሴት ይወክላል። በቋንቋህ ውስጥ ባል ለሚስቱ ሊጠቀም የሚችለው ጨዋነት ያለው ቃል ካለና እስካሁን በዚህ መጽሐፍ ካልተጠቀምክበት እዚህ ጋ ልትጠቀምበት ትችላለህ። ካልሆነም ባል ለሚስቱ ሊጠቀምበት የሚችለውን ሌላ የጨዋነት ቃል መጠቀም ትችላለህ። ይህንን በመኃልይ 4፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

አማና

x

ልቤን፤ በአንድ እይታ ብቻ፤ በአንድ ጌጥ ብቻ

“ልቤ፤ ማድረግ የሚኖርብሽ አንዴ ብቻ እኔን መመልከት ወይም አንድ ጌጥ ማሳየት ነው፝፝።” የሴቲቱ ዐይንና ጌጣጌጧ ሰውየውን ወደርሷ ስቧል።

የአንገት ሀብል

ይህ የአንገት ሀብል በአንገቷ ላይ ደጋግሞ ተጠምጥሞ ይሆናል።