am_tn/sng/04/08.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሰውየው ለሴቲቱ መናገሩን ይቀጥላል። እርሱ ሰው በማይኖርበት፣ አደገኛና እንግዳ በሆነ ቦታ ያሉ ይመስል የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለመፈጸም ነጻ ያለመሆናቸውን ይናገራል።

ከሊባኖስ

“ከሊባኖስ ወዲያ”

ሙሽራዬ

ይህ የዕብራይስጡ ቃል ያገባችን ሴት ወይም አንድ ሰው ወንድ ልጁን ለመዳር ያዘጋጃትን ሴት ይወክላል። በቋንቋህ ውስጥ ባል ለሚስቱ ሊጠቀም የሚችለው ጨዋነት ያለው ቃል ካለና እስካሁን በዚህ መጽሐፍ ካልተጠቀምክበት እዚህ ጋ ልትጠቀምበት ትችላለህ። ካልሆነም ባል ለሚስቱ ሊጠቀምበት የሚችለውን ሌላ የጨዋነት ቃል መጠቀም ትችላለህ።

አማና

በሰሜን እስራኤል የሚገኝ የተራራ ስም

ሳኔር

በአማና እና አርሞንዔም አቅራቢያ ያለ ተራራ ስም ነው። አንዳንድ ሰዎች ይህ ራሱን አርሞንዔም ተራራን እንደሚያመለክት ያስባሉ።

ዋሻ

እንደ ጎሬ ያለ ቦታ ወይም የተቦረበረ መሬት ሆኖ አንበሶችና ነብሮች የሚኖሩበት