am_tn/sng/04/06.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሰውየው ሴቲቱን ማድነቁን ይቀጥላል።

ንጋት እስኪሆንና ጥላዎቹ እስኪሸሹ ድረስ

በመኃልይ 2፡17 ያለውን ስንኝ እንደተረጎምከው በተመሳሳይ ቃላት ተርጉማቸው።

ወደ ከርቤ ተራራና ወደ ዕጣን ኮረብታ እሄዳለው

የ”ከርቤ ተራራ” እና “የዕጣን ኮረብታ” የሴቲቱን ጡቶች የሚገልፁ ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው። አ.ት፡ “የከርቤና የዕጣን ሽታ ያለባቸውን ተራሮች ወደሚመስሉት ጡቶችሽ ተጠግቼ እተኛለሁ” ወይም “ጣፋጭ ሽታ ወዳላቸው ጡቶችሽ ተጠግቼ እተኛለሁ” ወይም “ጣፋጭ ሽታ ወደሚሸቱት ተራሮች እሄዳለሁ”

የከርቤ ተራራ

“ከከርቤ የተሠራ ተራራ” ወይም “ከርቤ የሚበቅልበት ተራራ”

የእጣን ኮረብታ

“ከሚጨሰው የእጣን ጭስ የተነሳ በአየሩ ውስጥ የጭስ ደመና ያለበት ኮረብታ”

በሁሉም መልኩ ውብ ነሽ

“ሁሉም ክፍልሽ ውብ ነው” ወይም “ሁለመናሽ ውብ ነው”

የኔ ፍቅር

“አንቺ የምወድሽ”፣ ይህንን በመኃልይ 1፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ምንም እንከን የለብሽም

“ምንም የሚነቀፍ ነገር የለብሽም”