am_tn/sng/04/04.md

2.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሰውየው ሴቲቱን ማድነቁን ቀጥሏል።

አንገትሽ እንደ ዳዊት ግምብ ነው

ይህ እውነተኛ ግምብ ስለመሆኑ የሚያውቅ የለም። ግምብ ማለት ረጅምና ቀጭን ሕንጻ ሲሆን ዳዊት የገነባው መባሉ ውብ መሆኑን ያሳያል። ሰውየው የሴቲቱ አንገት ረጅም፤ ቀጭንና ውብ እንደሆነ ያስባል። አ.ት፡ “አንገትሽ እንደ ዳዊት ግምብ ረጅምና ያማረ ነው”

የዳዊት

“ዳዊት የገነባው”

በድንጋይ ድርድር የተገነቡ

ሴቶች ሙሉ አንገታቸውን የሚሸፍን የአንገት ሀብል ከጌጣጌጥ ድርድር ጋር ነበራቸው። ሰውየው እነዚህን የጌጣጌጥ ድርድሮች በግምቡ ላይ ካሉት የድንጋይ ድርድሮች ጋር ያነጻጽራቸዋል።

ከሺህ ጋሻ ጋር

ሰውየው በሴቲቱ የአንገት ሀብል ላይ ያሉትን ጌጣጌጦች በግምቡ ላይ ከተንጠለጠሉት ጋሻዎች ጋር ያነጻጽራቸዋል። የአንገት ሀብሏ አንገቷ ላይ ብዙ ዙር ዞሮ ይሆናል።

ሺህ ጋሻ

“1,000” ጋሻዎች

ሁሉም የወታደር ጋሻዎች

“የብርቱ ጦረኞች የሆኑ ጋሻዎች ሁሉ”

ሁለት ጡቶች

“ሁለት” የሚለው ቃል አላስፈላጊና ያለቦታው የገባ መስሎ ከታየህ ልታስወግደው ትችላለህ።

እንደ ሁለት የአጋዘን ግልገሎች፤ የአጋዘን መንታዎች

ሰውየው የሴቲቱ ጡቶች ተመሳሳይ፤ ለስላሳና ምናልባትም ትንንሽ እንደሆኑ ያመለክታል።

መንታዎች

ሁለት ልጆችን በአንድ ጊዜ የወለደች እናት፤ ልጆቹ መንታ ይባላሉ።

ሚዳቋ

አጋዘን የሚመስልና በፍጥነት የሚንቀሳቀስ እንስሳ ነው። ”አጋዘኖች” በመኃልይ 2፡7 እንዳለው በነጠላ ቁጥር ተርጉመው።

በተዋቡ አበቦች መካከል እየጋጠ

“በተዋቡ አበቦች መካከል እየተመገበ”፤ ሰውየው “በተዋቡ አበቦች መካከል እየጋጠ” የሚለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸምን የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም፤ እነዚህ ቃላት ምንን እንደሚያመለክቱ ግልፅ አይደለም። ቃል በቃል ቢተረጎሙ የተሻለ ይሆናል።

የተዋቡ አበቦች

ብዙ ውሃ ባለበት ስፍራ የሚበቅሉ መልካም መዓዛ ያላቸው አበቦች። በመኃልይ 2፡1 ላይ እንዳለው “አበባ” የሚለውን በብዙ ቁጥር ተርጉመው።