am_tn/sng/04/03.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሰውየው ሴቲቱን ማድነቁን ይቀጥላል

እንደ ደማቅ ቀይ ክር

ደማቅ ቀይ ውብ ቀለም ነው፤ ደማቅ ቀይ ክር ደግሞ በጣም ውድ ነበር። የሴቲቱ ከንፈሮች ቀይ ነበሩ። አ.ት፡ “እንደ ደማቅ ቀይ ክር ብስል ቀይ ናቸው” ወይም “ቀይና በጣም ውቦች ናቸው”።

ደማቅ ቀይ

ከደም ቀለም ጋር የሚመሳሰል ደማቅ ቀይ ቀለም

አስደሳች ነው

“ያማረ ነው”

እንደ ሮማን ክፋይ ናቸው

ሮማኖች ደማቅ ቀይ፣ ክብ እና ለስላሳ ናቸው። ሰውየው የሴቲቱ ጉንጮች ውቦችና እርሷም ጤነኛ መሆኗን እንደሚያሳዩ ያስባል። አ.ት፡ “እንደ ሁለት የሮማን ክፋዮች ቀይና ክብ ናቸው” ወይም “ቀይ፣ ሙሉና ጤናማ ናቸው”

ከአይነርግብሽ በስተጀርባ

ይህንን በመኃልይ 4፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።