am_tn/sng/04/02.md

1.2 KiB

ጥርሶችሽ በቅርቡ የተሸለቱ የሴት በጎች መንጋን ይመስላሉ

በጎች ከተሸለቱ በኋላ ይታጠባሉ፤ ቆዳቸውም በጣም ነጭ ሆኖ ይታያል። የሴቲቱም ጥርሶች ነጫጭ ናቸው።

በቅርቡ የተሸለቱ የሴት በጎች መንጋ

ይህ በገቢራዊነት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች ሱፋቸውን የሸለቷቸውን የሴት በግ መንጋ”

ከመታጠቢያ ስፍራ የሚመጡ

ሴቶቹ በጎች ከውሃው ውስጥ ወጥተው እየመጡ ነው። አ.ት፡ “ሰዎች ካጠቧቸው በኋላ ከውሃው ወጥተው እየመጡ ነው”

እያንዳንዱ መንታ አለው

በጎች አብዛኛውን ጊዜ በአንዴ ሁለት ግልገሎችን ይወልዳሉ። እነዚህ መንታዎች ብዙውን ጊዜ ይመሳሰላሉ። እያንዳንዱ የሴቲቱ ጥርስ በሌላ ጎን ካለው ጋር እኩል ነው።

ከመካከላቸው አንዱም አልጎደለም

እያንዳንዱ የሴቲቱ ጥርስ በሌላ ጎን ካለው ጋር እኩል ነው። ከጥርሶቿ አንድም የወለቀ የለም።

ሐዘንተኛ

የቅርብ ሰው የሞተበት