am_tn/sng/02/16.md

2.0 KiB

ወዳጄ የእኔ ነው

“ውዴ የኔ ነው”

ወዳጄ

ይህ ሐረግ ሴቲቱ የምትወደውን ሰውዬ ያመለክታል። በአንዳንድ ቋንቋዎች ሴቲቱ “የኔ አፍቃሪ” ብትለው በይበልጥ የተለመደ ይሆን ይሆናል። ይህንን በመኃልይ 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእኔ ውድ” ወይም “የእኔ አፍቃሪ”።

እኔ የእርሱ ነኝ

“እኔ የእርሱ ነኝ”

ያሰማራል

“ይመግባል” ወይም “ሳር ይበላል”። ሴቲቱ ሰውየውን በአበቦች መሐከል እፅዋትን እንደሚመገብ “ሚዳቋ ወይም የአጋዘን ግልገል” አድርጋ ትናገራለች። መሰማራት ምናልባት የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸምን የሚገልፅ ዘይቤአዊ አነጋገር ሊሆን ይችላል።

የተዋቡ አበቦች

ብዙ ውሃ ባለበት ቦታ የሚበቅሉ ባለጣፋጭ ሽታ አበቦች። በመኃልይ 2፡1 እንዳለው “ውብ አበቦች” ብለህ በብዙ ቁጥር ተርጉመው።

ንጋት

ፀሐይ የምትወጣበት የቀኑ ክፍል

ጥላዎቹ ሸሽተዋል

ሴቲቱ ጥላዎቹ ከፀሐይ ብርሐን እየሸሹ እንዳሉ አድርጋ ትገልፃቸዋለች። አ.ት፡ “ጥላዎቹ ጠፍተዋል”

እንደ ሚዳቋ ወይም የአጋዘን ግልገል

ይህንን በመኃልይ 2፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ሚዳቋ

እነዚህ እንስሶች አጋዘን የሚመስልና በፍጥነት የሚንቀሳቀስ እንስሳ ነው። በመኃልይ 2፡7 ላይ እንዳለው “ሚዳቋዎች” በነጠላ ቁጥር ተርጉመው።

ወንድ አጋዘን

ጎልማሳ ወንድ አጋዘን

ወጣ ገባ ያለባቸው ተራሮች

“አለታማ ተራሮች” ወይም “ አስቸጋሪ ተራሮች”