am_tn/sng/02/15.md

1.9 KiB

ያዙ

ይህ ሴቲቱ ከአንድ በላይ ለሆኑ ወንዶች የምትናገር ይመስል ብዙ ቁጥር ነው፤ ነገር ግን አብዛኛዎቹ ትርጉሞች ለሰውየው እንደምትናገር አድርገው ይተረጉሙታል፣ ስለዚህ በነጠላ ልትተረጉመው ትችላለህ።

ቀበሮዎቹ

እነዚህ እንስሶች ትናንሽ ውሾችን የሚመስሉ ሲሆኑ በፍቅር ስነ-ግጥም ውስጥ ብዙ ጊዜ ወጣት ሴትን ሊያባልጉ የሚችሉ ጉጉ ወጣት ወንዶችን እንዲወክል ጥቅም ላይ ውለዋል።

የኛ የወይን ቦታ … ለኛ

“እኛ” እና “ለኛ” የሚሉት ቃላት ሊሆኑ የሚችሉት 1) በመኃልይ 1፡4 እንዳለው ሌላውን ሳይሆን ሴቲቱን ራሷን የሚያመለክት ወይም 2) ሴቲቱንና ሰውየውን የሚያካትት ወይም 3) ሌሎችን ሳያካትት ሴቲቱንና የተቀሩትን ቤተሰቦቿን የሚያመለክት ይሆናል።

ቀበሮዎች

ሌላው ትርጉም ሊሆን የሚችለው “የጫካ ውሻ” ነው። የጫካ ውሻ ረጃጅም እግሮች ያሉት ቀጭን የውሻ አይነት ነው።

የሚያበላሹ ትናንሽ ቀበሮዎች

ቀበሮዎች ጉድጓድ በመቆፈርና የወይን ፍሮዎችን በመብላት የወይን ተክሎችን ያበላሻሉ። ይህ ወጣት ሴቶችን የሚያባልጉ ወጣት ወንዶችን የሚገልፅ ዘይቤአዊ አነጋገር ሊሆን ይችላል።

በማበብ ላይ

ይህ የሚያመለክተው የወይኑ ቦታ ጤናማ እንደሆነና ወይኑም ማፍራቱን ነገር ግን ለመበላት ዝግጁ አለመሆናቸውን ያመለክታል። ይህ ለማግባትና ልጆችን ለመውለድ የደረሰችን ወጣት ሴት የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ሊሆን ይችላል።