am_tn/sng/02/10.md

1.7 KiB

ወዳጄ

ይህ ሐረግ ሴቲቱ የምትወደውን ሰውዬ ያመለክታል። በአንዳንድ ቋንቋዎች ሴቲቱ “የኔ ፍቅር” ብትለው በይበልጥ የተለመደው አገላፅ ይሆናል። ይህንን በመኃልይ 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእኔ ውድ” ወይም “የእኔ አፍቃሪ”።

የኔ ፍቅር፣ ተነሺ

“የኔ ፍቅር ከአልጋሽ ተነሺ”

የኔ ፍቅር

“አንቺ፣ የምወድሽ”። ይህንን በመኃልይ 1፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ተመልከቺ

“በጥሞና አድምጪ” ወይም “ልናገር ያለሁት ጠቃሚ ነገር ነው”። በቋንቋህ አድማጭ በጥሞና እንዲያዳምጥ የሚያሳስበውን ቃል መጠቀም ትችላለህ።

ክረምቱ አልፏል፣ ዝናቡም አልፎ ሄዷል

በክረምት ከቤት ውጪ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለመፈጸም እጅግ ቀዝቃዛና እርጥበታማ ነው፣ ነገር ግን የቅዝቃዜውና የእርጥበቱ ጊዜ አልፏል።

ክረምቱ አልፏል

ክረምት እፅዋት የማያድጉበትና ሰዎች ቤታቸው ውስጥ ለመቆየት የሚመርጡበት የአመቱ ቀዝቃዛ ወቅት ነው። በዓመቱ ውስጥ ስላለው ስለዚያ ወቅት በቋንቋህ መጠቀም ትችላለህ።

ዝናቡ አልፎ ሄዷል

በእስራኤል ዝናብ የሚዘንበው በክረምት ብቻ ነው። እዚህ ጋ የተገለፀው የሚያረሰርስ የሙቀት ወቅት ዝናብ ሳይሆን ደስ የማይልና ቀዝቃዛ ዝናብ ነው።