am_tn/sng/02/08.md

4.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

የመጽሐፉ ሁለተኛው ክፍል እዚህ ይጀምራል።

አጠቃላይ መረጃ

ሴቲቱ የምታወራው ለራሷ ወይም ለኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች መሆኑ ግልፅ አይደለም።

አድምጡ

ትርጓሜዎች ሊሆኑ የሚችሉት 1) “ልናገር ያለሁትን በጥንቃቄ አድምጡ”። በራስህ ቋንቋ አድማጮች በጥሞና እንዲያደምጡ የሚናገር ቃል ልትጠቀም ትችላለህ፣ ወይም 2) “ሲመጣ መሰማት እንድትችሉ አድምጡ”

ወዳጄ

ወዳጄ ይህ ሐረግ ሴቲቱ የምትወደውን ሰውዬ ያመለክታል። በአንዳንድ ቋንቋዎች ሴቲቱ አገላፅ “የኔ አፍቃሪ” ብትለው በይበልጥ የተለመደ ይሆናል። ይህንን በመኃልይ 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእኔ ውድ” ወይም “የእኔ አፍቃሪ”።

እየተወረወረ … እየዘለለ … እያየ… አተኩሮ እየተመለከተ

ሴቲቱ ሰውየው መምጣቱን ስታይ በመደነቅ የሚያደርገውን በተቻላት መጠን በጥቂት ቃላት ትገልፃለች። የአንተ ቋንቋ፣ ተናጋሪው ሊሆን ስላለ ነገር የሚደነቅበትን ስሜት የሚያሳይበት የተለየ አገላለፅ ይኖረው ይሆናል።

በተራሮች ላይ እየተወረወረ፣ በኮረብታዎች ላይ እየዘለለ

“በተራሮች ላይ እየተወረወረ፣ በኮረብቶች ላይ በፍጥነት እየሮጠ”። ሰውየው እንደ፝ “ሚዳቋ ወይም ወንድ አጋዘን” በአስቸጋሪ መሬት ላይ በፍጥነት ወደ እርሷ እንደሚመጣ ሴቲቱ ትናገራለች (ቁ. 9)።

እንደ ሚዳቋ ወይም የአጋዘን ግልገል

ሚዳቋ እና የአጋዘን ግልገል አስቸጋሪ መሬት ላይ በፍጥነት መንቀሳቀስ ይችላሉ። ሰውየው ከእርሷ ጋር ለመሆን በተቻለው ፍጥነት እንደሚመጣ ሴቲቱ ታስባለች። በቋንቋህ ሰዎች ፈጣን ነው ብለው የሚያስቡትን እንስሳ ተጠቅመህ መተርጎም ትችላለህ።

ሚዳቋ

ይህ አጋዘን የሚመስልና በፍጥነት የሚንቀሳቀስ እንስሳ ነው። ”አጋዘኖች” የሚለውን በመኃልይ 2፡7 እንዳለው በነጠላ ተርጉመው።

የአጋዘን ግልገል

“ተባእት የአጋዘን ግልገል”

ተመልከቺ

“በጥንቃቄ አድምጪ” ወይም “ልናገር ያለሁት ጠቃሚ ነገር ነው”። አድማጭ በጥሞና እንዲያዳምጥ የሚያሳስብ ቃል በራስህ ቋንቋ መጠቀም ትችላለህ።

ከግምባችን በስተጀርባ

“በግንባችን በሌላኛው ጎን”። ሴቲቱ ቤት ውስጥ ስትሆን ሰውየው ከቤት ውጪ ነው።

የኛ ግንብ

“የኛ” የሚለው ቃል ሴቲቱንና አብረዋት በቤት ያሉ ሌሎች ሰዎችን ያመለክታል። ሴቲቱ ከራሷ ጋር የምታወራ ከሆነ አካታች ነው፣ ነገር ግን ለኢየሩሳሌም ሴት ልጆች የምትናገር ከሆነ፣ ራሷንና ጓደኞቿን ወይም ራሷን በብዙ ቁጥር የምታመለክት ከሆነ ፥ እንደ “ደስ ተሰኝተናል” … “ሐሴት እናደርጋለን” … “እንደሰት” የማያካትት ይሆናል።

በመስኮት አሻግሮ እየተመለከተ

“በመስኮቱ በኩል አተኩሮ ይመለከታል”

በርብራቡ መካከል አጮልቆ እየተመለከተ

“በርብራቡ መካከል ሰረቅ አድርጎ ያያል ”

ርብራብ

ረዘም ረዘም ያሉ እንጨቶችን አንድ ላይ በመሰካካት የተሰራ የመስኮት ወይም ሌላ በር መከለያ ነው። ርብራብ ሰዎች አጮልቀው ማየት የሚችሉበት ክፍተት አለው።