am_tn/sng/02/07.md

1.5 KiB

የኢየሩሳሌም ሴት ልጆች

“የኢየሩሳሌም ወጣት ሴቶች”። እነዚህ ወጣት ሴቶች አብረዋት ስላልነበሩ ሊሰሟት አይችሉም፣ እርሷ ግን አብረዋት እንዳሉና እንደሚሰሟት አድርጋ ትናገራለች።

በሚዳቆዎቹና በሜዳ ባሉ አጋዘኖች

የኢየሩሳሌም ሴቶች ሊሰሟት ባይችሉም፥ ሴቲቱ እንደሚሰሟት አድርጋ ቃላቸውን ቢያፈርሱ ሚዳቋዎቹ እና አጋዘኖቹ እንደሚቀጧቸው ትናገራለች።

ሚዳቆዎቹ

እነዚህ አጋዘን የሚመስሉና በፍጥነት የሚንቀሳቀሱ እንስሶች ናቸው።

ሴት አጋዘን

ሴት አጋዘን

የሜዳ

“በገጠር የሚኖሩ”። ይህ ታርሶ የማያውቅ ምድር ነው።

እርሷ እስክትፈልግ ድረስ ፍቅርን አትቀስቅሱ ወይም አታነሣሡ

እዚህ ጋ “ፍቅር” መቀስቀስ እንደማይፈልግ የተኛ ሰው ተደርጎ ተነግሮለታል። ሰውየው እና ሴቲቱ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጽመው እስኪጨርሱ ድረስ መታወክ እንደማይፈልጉ የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው።

አትቀስቅሱት ወይም አታነሣሡት

ቋንቋህ ሰዎችን ክእንቅልፍ ለማስነሣት አንድ ቃል ብቻ ካለው ሁለቱን ቃላት ማዋሀድ ትችላለህ። አ.ት፡ “አታንቁት”