am_tn/sng/02/03.md

2.8 KiB

ወጣት ወንዶች … እንደ እንኮይ ዛፍ

ሰዎች የእንኮይ ዛፍ ፍሬን ይወዳሉ፣ ነገር ግን ሌሎች የዱር ዛፎች ፍሬ አያፈሩም። ሴቲቱ ከሌሎች ወንዶች ይልቅ ከሰውየው ጋር መሆን ያስደስታታል።

የእንኮይ ዛፍ

ቢጫ እና በጣም ጣፋጭ ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ ነው። አንባቢዎችህ ይህ ምን እንደሆነ የማያውቁ ከሆኑ በሌላ የፍራፍሬ ዛፍ ስም ወይም “የፍራፍሬ ዛፍ” በሚል ጥቅል ቃል ልትተካው ትችላለህ።

ጫካው

እዚህ ጋ፣ የዕብራይስጡ ቃል ሰዎች የማይጠቀሙበት ፥ ዛፎች የሚበቅሉበት ስፍራ ይለዋል።

ወዳጄ

ይህ ሀረግ ሴቲቱ የምትወደውን ሰውዬ ያመለክታል። በአንዳንድ ቋንቋዎች ሴቲቱ “የኔ አፍቃሪ” ብትለው በይበልጥ የተለመደ ይሆን ይሆናል። ይህንን በመኃልይ 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእኔ ውድ” ወይም “የኔ አፍቃሪ”

ከጥላው በታች በታላቅ ደስታ እቀመጣለሁ

ሴቲቱ ከሰውየው አጠገብ በመሆኗ ሀሴት እና መፅናናትን አግኝታለች።

ፍሬው ለምርጫዬ ጣፋጭ ነው

ሴቲቱ ጣፋጭ ፍሬ በመመገብና በሰውየው አጠገብ በመሆን ትደሰታች።

የወይን ቤት

ትርጉሞቹ 1) ንጉሱ ለብዙ ሰዎች ወይንና ብዙ ምግብ የሚያቀርብበትን ሰፊ ክፍል ወይም 2) ሴቲቱ እና ሰውየው ብቻቸውን ሊሆኑ የሚችሉበት በወይን ተክል ውስጥ ያለ ትንሽ ዳስ

በኔ ላይ ያለው አላማው ፍቅር ነበር

በኔ ላይ ያለው አላማው ፍቅር ነበር ትርጉሞቹ 1) ሰንደቅ አላማ ለወታደራዊ አጀብ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። ወታደራዊ አጀቡ፣ ንጉሱ ብዙ ሰዎችን ወደሚመግብበት ትልቅ ክፍል ውስጥ ለመግባት የፈራችውን ሴት የሚያበረታ የሰውየውን ፍቅር የሚወክል ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ነገር ግን የፍቅር ጥበቃው መራኝ፣ ብርታትንም ሰጠኝ” ወይም 2) ሰውየው ክእርሷ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለመፈጸም መፈለጉን ሴቲቱ ከአስተያየቱ ተረዳች። አ.ት፡ “በፍቅር ዐይን አየኝ” ወይም “ባየኝ ጊዜ ከእኔ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለመፈጸም መፈለጉን አውቄአለሁ” ወይም 3) የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸሙ። አ.ት፡ “በፍቅር ሸፈነኝ”