am_tn/rut/03/01.md

1.7 KiB

አማቷ

ኑኃሚን የሩት ሟች ባል እናት ናት

ልጄ

ሩት የኑኃኒንን ልጅ በማግባት ብሎም አብራት ወደ ቤተልሔም በመመለስ የኑኃሚን ልጅ ሆናለች።

የሚመችሽን ቤት እንድፈልግልሽ አይገባኝምን?

“መልካም እንዲሆንልሽ እረፍት አልፈልግልሽም?” ኑኃሚን ይሄንን ጥያቄ በመጠየቅ ያቀደችላትን ለመናገር ትጠቀምበታለች። “እረፍት የመታረጊበትን ቦታ ልፈልግልሽ ይገባኛል” ወይንም “ የሚንከባከብሽ ባል ልፈልግልሽ ይገባኛል።”

የምታርፊበት ቦታ

ትርጉሙ ሊሆን የሚችለው፤ 1) በቀጥታ የምትኖርበትን ቤት ማግኘት ወይንም 2) በማስጠጋት ረገድ የሚንከባከባት ባል ስለመፈለግ። ኑኃሚን ሁለቱንም ማለት ፈልጋ ሊሆንም ይችላል።

ከሴቶች ሠራተኞቹ ጋር አብረሽ የነበርሽበት

የዚህ ግልፅ ትርጉም ከሴቶቹ ጋር እየሰራች እንደነበረ ሊያሳይ ይገባል። “ከገረዶቹ ጋር የለበርሽበት።”

ዘመዳችን አይደለምን?

ኑኅሚን ከዚህ በፊት ለሩት የነገረቻትን ነገር እያስታወሰቻት ነው የሚሆነው። “እርሱ ዘመዳችን ነው።”

አሁንም

“ልብ በይ።” ከዚህ በኋላ የምትላትን ነገር እንድታስተውል እያመለከቻት ነው።

ያበራል

“በመንሽ ይበትናል” ይህ በንፍስ ድጋፍ ሰብሉን ከገለባው የመለየት ሂደት ነው።