am_tn/rut/01/19.md

1.7 KiB

እንደ ደረሱም

“እንዲህ ሆነ።” ይህ የታሪኩ አዲስ ምዕራፍ መነሻ አመላካች ነው።

ከተማው በሙሉ

“ከተማው” የሚለው በዛ የሚኖሩ ሰዎችን በሙሉ ያመላክታል። “የከተማይቱ ሰዎች ሁሉ።”

ይህች ኑኃሚን ናትን?

ኑኃሚን በቤተልሔም ከኖረች በዙ ዓመታትን አስቆጥሯል በሎም ባሏ እና ወንድ ልጆቿ አብረዋ አልነበሩም፤ እናም በዛ የነበሩት ሴቶች ኑኃሚን ስለመሆኗ መጠራጠራቸውን የሚያመናክት እባባል ነው። እንደ እውነተኛ ጥያቄ ቁጠሩት።

ኑኃሚን ብላችሁ አትጥሩኝ

“ኑኃሚን” የሚለው ስም “የእኔ ደስታ” የሚል ትርጉም ነው ያለው። ኑኃሚንም ባሏን እና ልጆቿን ስላጣች፤ ስሟ ሕይወቷን እንደሚመጥን አይሰማትም።

ማራ

መራራ፤ የስሙ ትርጉም ሲሆን፤ ብዙውን ግዜ ይህ ስም ሲተረጎም እንደሚያወጣው ስም “ማራ” ተበሎ ይተረጎማል።

በሙላት ወጣሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ባዶዬን መለሰኝ

ኑኃሚን ከቤተልሔም ስትወጣ በልዋ እና ሁለት ወንዶች ልጆችዋ በሕይወት ነበሩ፤ ደስተኛም ነበረጭ ኑኃሚን ለባልዋ እና ሁለት ልጆችዋ ሞት ተጠያቂ የምታደርገው እግዚአብሔርን ነው። ወደ እስራኤልም ብቻዋን እንድትመለስ ያደረገው እርሱ ነው።

አስጨንቆኛል

“ፍርድን አሳልፎብኛል።”

አዋርዶኛል

መከራ አምጥቶብኛል