am_tn/rut/01/16.md

1.0 KiB

ወደ ምትሄጅበት

“ወደ ምትኖሪበት”

ሕዝብሽ ሕዝቤ

ሩት በዚህ የምታመላክተው የኑኃሚንን ህዝቦች ነው፤ እስራኤላውያንን። “የአገርሽን ሕዝቦች እንደ እራሴ ሕዝቦች እቆጥራለሁ።” ወይንም “ዘመዶችሽን እንደ ዘመዶቼ እቆጥራለሁ።”

በምትሞቺበት እሞታለሁ

ይህ ሩት እስከ ዕድሜዋ ፍፃሜ ከኑኃሚን ጋር በአንድ ቦታ እና ከተማ የመሆን ፍላጎቷን ያሳያል።

ብለይሽ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ፤ ከዚህም የከፋ ያድርግብኝ።

ይህ የሚያመላክተው ሩት አደርጋለሁ ያለችውን ባታደርግ፤ እግዚአብሔር እንዲቀጣት እየጠየቀች እንደሆነ ነው። “እግዚአብሔር አይፍቀድ እንደማለት ነው።”

ከመናገር ዝም አለች

“ኑኃሚን ሩትን መጐትጐቷን ተወች”