am_tn/rut/01/11.md

1.9 KiB

ከእኔ ጋር ለምን ትሄዳላችሁ?

ይህ ምላሽ የሚሰጥለት ጥያቄ አይነት አይደለም። “ከእኔ ጋር መሄዱ ትርጉም አይሰጥም።” ወይንም “ከእኔ ጋር መሄድ የለባችሁም።”

ባል የሚሆኗችሁ ሌሎች ልጆች ከእንግዲህ የምወልድ ይመስላችኋልን?

ኑኃሚን በዚህ ጥያቄዋ ለእነርሱ የሚሆኑ ወንድ ልጆች ከዚህ ወድያ ልትወልድላቸው እንደማትችል ትናገራለች። “መቼስ ለእናንተ ባል መሆን የሚችሉ ሌሎች ወንድ ልጆች ከዚህ በኋላ መውለድ አልችልም።”

ባል እንዳላገባ እጅግ አርጅቻለሁ

ባል የማግባቱ ምክንያት በግልፅ ተጠቅሷል። “ሌሎች ወንድ ልጆች እንዳልወልድ”

ልጆች ብወልድ

“መፀነስ” ወይንም “ወንድ ልጆች መውለድ”

እስኪያድጉ ድረስ ትጠብቃላችሁን? እነርሱን በመጠበቅ እስከዚያ ሳታገቡ ትቈያላችሁን?

እነኚህ ምላሽ የሚሰጥላቸው ጥያቄዎች አይነት አይደሉም። “ታገብዋቸው ዘንድ እስኪያድጉ አትጠብቋቸውም። አሁን ማግባትን ትመርጣላችሁ”

ሁኔታው ከእናንተ ይልቅ ለእኔ እጅግ መራራ ነው

መራራነት የሃዘን እና የሰቆቃ መገለጫ ነው፤ በዚህም የሃዘንዋ መንሳኤ ምን እንደሆነ ማወቁ አያዳግትም። “የእናንተ ባል አለመኖር እኔን ያሳዝነኛል።

የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ተነሥቶአልና

“እጅ” የሚለው የእግዚአበሔርን ኃይል ወይንም ተፃዕኖ ያሳያል። “የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ወጥቶአልና።”