am_tn/rut/01/08.md

1.9 KiB

ምራቶች

የወንድ ልጆች ሚስቶች ወይንም የወንድ ልጆቿ መበለቶች

እያንዳንዳችሁ

ኑኃሚን የምታዋራው ሁለት ሰዎችን ነበር፤ ከዚህ በመቀጠልም እናንተ ብላ ስትናገር ሁለቱን በማስመልከት ነው።

ወደ እናቶቻችሁ ቤት

“ወደ እናቶቻችሁ ቤትም”

በጎ ነገር እንዳደረጋችሁ

“ቸርነትን እንዳደረጋችሁ”

በጎነት

“ቸርነት” የ ፍቅር፣ የበጎነት፣ እና ታማኝነትን ያመላክታል።

ለሞቱት

“ለሞቱት ባሎቻችሁ” ን ኡኃሚን በዚህ የሞቱትን ልጆችዋን ማመላከት ነው የፈለገችው።

ያድርግላችሁ

“እንደዚሁ ያድርግላችሁ” ወይንም “እንዲደረግላችሁ ይፍቀድ”

ያሳሪፋችሁ

እዚህ ጋር “ያሳርፋችሁ” የሚለው በትዳርም የሚገኘውን ደህንነትን ያጠቃልላል።

በምታገቡት ባል ቤት

ከአዳዲስ ባሎቻችሁ፣ ከሌላ ሰው ባል ጋር አይደለም። ይሄ የሚያመላክተው በባልየው ቤት ውስጥ እና ከባልየው የሃፍረት ከለላ ስር ማለት ነው።

እነርሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ

ድምፅን ከፍ ማድረግ ለጮክ በሎ ማውራትን የሚያመላክት አባባል ነው። ምራቶቷም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ወይንም አምርረው አለቀሱ።

ተመልሰን … እንሄዳለን

“እንመለሳለን” ዓርፋ እና ሩት “እኛ” ብለው ሲናገሩ ስለራሳቸው እንጂ ስለ ሩት አንነበረም የሚናገሩት።

ከአንቺ ጋር

እዚህ ጋር “አንቺ” የሚለው የሚያመላክተው ኑኃሚንን ነው።