am_tn/rom/16/25.md

2.9 KiB

አያያዥ ሀሳብ፦

ጳውሎስ መልዕክቱን በበረከት ጸሎት ይዘጋል።

እንግዲህ

እዚህ ላይ “እንግዲህ” የሚለው ቃል የደብዳቤውን መጨረሻ ክፍል ያመለክታል። ይህን በራሳችሁ ቋንቋ መግለጽ የምትችሉ ከሆነ እሱን መጠቀም ይቻላል።

ሊያቆማችሁ የሚችለው

ጳውሎስ እዚህ ላይ ጠንካራ እምነት መኖርን ልክ ከመውደቅ ይልቅ እንደመቆም አድርጎ ይስለዋል። አማራጭ ትርጉም፡- “እምነታችሁን ለማበርታት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ እኔ ወንጌልና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ስብከት

“ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሰበክሁት እንደ የምስራቹ ቃል”

ለረጅም ጊዜ ተሰውሮ ቆይቶ መገለጥን ባገኘው ሚስጥር

ጳውሎስ እግዚአብሔር ቀድመው ተሰውረው የቆዩ ነገሮችን ለአማኞች እንደገለጠ ይናገራል። እነዚህ ነገሮች ሚስጥር እንደነበሩ አድርጎ ይናገራል። ይህን በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መተርጎም ትችላለህ። አማራጭ ትርጉም፡- “ምክንያቱም እግዚአብሔር ለእኛ ለአማኞች ለረጅም ጊዜ ሚስጥር ሆኖ የጠበቀውን ነገር ስለገለጠልን” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን አሁን በዘላለማዊው በእግዚአብሔር ትዕዛዝ በነቢያት ጽሁፎች ለሁሉም ሕዝቦች ተገልጧል፣ እንዲታወቅም ሆኗል

“ተገልጧል” እና “እንዲታወቅ ሆኗል” የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው። ጳውሎስ ሁለቱንም የሚጠቀመው አጽንዖት ለመስጠት ነው። እነዚህን ቃላት አንድ ላይ በማድረግ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መተርጎም ትችላለህ። አማራጭ ትርጉም፡- “አሁን ግን ዘላለማዊው እግዚአብሔር በነቢያቱ ጽሁፍ አማካይነት ለሕዝብ ሁሉ እንዲታወቅ አድርጓል” (ጥምር ቃል እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የእምነት መታዘዝን እንዲያመጣ

እዚህ ላይ “መታዘዝ” እና “እምነት” የሚሉት ቃላት ረቂቅ ስሞች ናቸው። “ታዛዥነት” እና “መታመን” የሚሉትን በትርጉምህ ላይ መጠቀም ትችላለህ። አማራጭ ትርጉም፡- “ሕዝብ ሁሉ እግዚአብሔርን ስለሚታመኑት እንዲታዘዙት” (ረቂቅ ስሞች እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)