am_tn/rom/16/17.md

3.3 KiB

አያያዥ ሀሳብ፦

ጳውሎስ ለአማኞች ስለ አንድነትና ለእግዚአብሔር ስለመኖር አንድ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል።

ወንድሞች

ይህ ሌሎች ክርስቲያኖችን ሲያመለክት፣ ወንዶችና ሴቶችን ያካትታል

እንድታስቡ

“እንድትጠነቀቁ”

መከፋፈልንና ማሰናከያን የሚያደርጉ

ይህ የሚያመለክተው ክርክርን የሚፈጥሩ ሰዎችንና፣ ሌሎችን በኢየሱስ እንዳያምኑ ምክንያት የሚሆኑትን ሰዎች ነው። አማራጭ ትርጉም፡- “አማኞች እርስ በርስ እንዲከራከሩና በእግዚአብሔር እምነት እንዳይኖራቸው የሚያደርጉ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከተማራችሁት ትምህርት ወጥተው ሄደዋል

“እናንተ ከተማራችሁት እውነት ጋር የማይስማማ ትምህርት ያስተምራሉ”

ከእነርሱ ራቁ

“ራቁ” ማለት “አትስሟቸው” የሚለውን ትርጉም የያዘ ዘይቤ ነው። አማራጭ ትርጉም፡- “አታዳምጧቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ለገዛ ሆዳቸው እንጂ

“ያገለግላሉ” የሚለው ቃል ከላይ ካለ ሐረግ አገባብ ትርጉሙን መረዳት ይቻላል። ይህ በተለይ አረፍተ ሃሳብ መገለጽ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “ይልቁንም የራሳችውን ሆድ ነው የሚያገለግሉት” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን ለገዛ ሆዳቸው

“ሆድ” የሚለው ቃል የአካላዊ ፍላጎቶችን የሚያሳይ ምትክ ስም ነው። የገዛ ሆዳቸውን ማገልገል ማለት ፍላጎቶቻቸውን ማግኘት ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን የራሳቸውን ራስ ወዳድ የሆኑ ፍላጎቶች ብቻ ማግኘት ነው የሚፈልጉት” (ምትክ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በለስላሳና መልካም ንግግራቸው

“ለስላሳ” እና “መልካም” የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም አላችው። ጳውሎስ እነዚህ ሰዎች እንዴት አማኞችን እያታለሉ እንደሆነ አጽንዖት ይሰጣል። አማራጭ ትርጉም፡- “መልካምና እውነት የሚመስሉ ነገሮችን በመናገር” (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

የንጹሃንን ልብ ያታልላሉ

እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው የአንድን ሰው አእምሮ ወይም ውስጣዊ ማንነት የሚወክል ምትክ ስም ነው። አማራጭ ትርጉም፡- “ንጹሃን አማኞችን ያታልላሉ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ንጹሃን

ይህ ገር፣ ብዙ የማያውቁና የዋህ አማኞችን ያመለክታል። አማራጭ ትርጉም፡- “በየዋህነት የሚያምኗቸውን” ወይም “እነዚህ አስተማሪዎች እያታለሏቸው እንደሆነ የማያውቁትን”