am_tn/rom/16/01.md

2.0 KiB

አያያዥ ሀሳብ፦

ከዚህ በኋላ ጳውሎስ በሮሜ ያሉት አማኞችን ብዙዎቹን ስማቸውን እየጠራ ሰላምታን ያቀርባል።

ፌበንን አደራ እላችኋለሁ

“ፌበንን እንድታከብሯት እፈልጋለሁ”

ፌበን

ይህ የአንዲት ሴት ስም ነው። (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል እና የማይታወቁትን ተርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

እኅታችንን

“እኅታችንን” የሚለው ቃል ውስጥ ያለው የባለቤት አመልካች “እኛ” ጳውሎስንና ሌሎች ሁሉንም አማኞች ይወክላል። አማራጭ ትርጉም፡- “በክርስቶስ እህታችን” (አካታች “እኛ” የሚለውን ይመልከቱ)

ክንክራኦስ

ይህ በግሪክ የሚገኝ የወደብ ከተማ ነው። (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል እና የማይታወቁትን ተርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

በጌታ ስም ተቀበሏት

ጳውሎስ በሮሜ የሚገኙ አማኞች ፌበንን እንደ አጋር አማኝ እንዲቀበሏት ያበረታታቸዋል። አማራጭ ትርጉም፡- “ተቀበሏት፣ ምክንያቱም ሁላችንም የጌታ ነንና“ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለቅዱሳን በሚመጥን መንገድ

“አማኞች ሌሎች አማኞችን መቀበል ባለባቸው መንገድ”

አጠገቧ ቁሙ

ጳውሎስ የሮሜን አማኞች ለፌበን የሚያስፈልጋትን ነገር በሙሉ እንዲሰጧት ያበረታታቸዋል። አማራጭ ትርጉም፡- “የሚያስፈልጋትን ሁሉ በመስጠት እርዷት” (ለስላሴ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ለብዙዎች ለእኔም ጨምሮ ረዳት ነበረችና

“ብዙ ሰዎችን ረድታለች፣ እንዲሁም እኔንም ረድታኛለች”