am_tn/rom/15/30.md

1.7 KiB

እነሆ

ይህ ጳውሎስ ይተማመንባቸው ስለነበረው ስለ መልካም ነገሮች (ሮሜ 15:29) ማውራት አቁሞ ሊጋፈጣቸው ስላሉት ነገሮች ማውራት መጀመሩን የሚያሳይ ነው። ቋንቋችሁ ይሄንን የማሳያ መንገድ ካለው እዚህ ላይ ጥቅም ላይ አውሉት።

አነሳሳችኋለሁ

“አበረታታችኋለሁ”

ወንድሞች

ይህ ሌሎች ክርስቲያኖችን ያመለክታል፣ ሴቶችንና ወንዶችን ያካትታል

እንድትተጉ

“በርትታችሁ እንድትሰሩ” ወይም “እንድትታገሉ”

ከማይታዘዙት እድን ዘንድ

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “ከማይታዘዙት እግዚአብሔር ያድነኝ ዘንድ” ወይም “የማይታዘዙት እንዳይጎዱኝ እግዚአብሔር ከእነርሱ ያድነኝ ዘንድ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በኢየሩሳሌም የሚኖረኝ አገልግሎት በአማኞች ዘንድ ተቀባይ እንዲሆን

እዚህ ላይ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ያሉ አማኞች ከመቄዶንያና ከአካይያ አማኞች ይዞ የመጣውን ገንዘብ በደስታ እንዲቀበሉት ያለውን ፍላጎት ያሳያል። አማራጭ ትርጉም፡- “የምወስድላቸውን ገንዘብ በኢየሩሳሌም ያሉ አማኞች በደስታ እንዲቀበሉኝ ጸልዩ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)