am_tn/rom/15/22.md

1018 B

አያያዥ ሀሳብ፦

ጳውሎስ በሮም ላሉ አማኞች እነርሱን ለመጎብኘት ስላለው የግል ሃሳብ ይነግራቸዋል፣ እንዲሁም አማኞቹን እንዲጸልዩ ይነግራቸዋል።

እንዲሁም ተከለከልሁ

ይህን በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መተርጎም ትችላለህ። አማራጭ ትርጉም፡- “ከለከሉኝ” ወይም “ሕዝቡ ከለከሉኝ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚህ በኋላ በነዚህ ቦታዎች ስፍራ የለኝም

ጳውሎስ እዚህ ላይ ለማለት የፈለገው በነዚህ ስፍራዎች ሰዎች ስለ ክርስቶስ ያልሰሙበት ቦታ የለም ነው። አማራጭ ትርጉም፡- “በእነዚህ ቦታዎች ሰዎች ስለ ክርስቶስ ያልሰሙበት ስፍራ የለም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)