am_tn/rom/15/17.md

1.4 KiB

ምንም ነገር ልናገር አልደፍርምና … እነዚህ ነገሮች በሙሉ በቃልና በስራ፣ በምልክትና በድንቅ ነገር ኃይል፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይልም ተሰርተዋል

እዚህ ላይ ያለውን መንትያ አሉታዊ መግለጫ በአዎንታዊ መግለጫ መተርጎም ይቻላል። እዚህ ላይ “እነዚህ ነገሮች” የሚለው ክርስቶስ በጳውሎስ በኩል ያሳካቸውን ነገሮች ነው። አማራጭ ትርጉም፡- “አሕዛብ እንዲታዝዙ፣ ክርስቶስ ብቻ በእኔ በኩል በቃሌና በስራዬ ፣ በምልክትና በድንቅ ነገር ኃይል በመንፈስ ቅዱስም ኃይል ያደረገውን ነገር እናገራለሁ” (መንትያ አሉታዎች እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ምልክትና ድንቅ ነገር

እነዚህ ሁለት ነገሮች ተመሳሳይ ትርጉምን የያዙ ሲሆን የተለያዩ ተዓምራትን ያመለክታሉ። (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ስለዚህ ከኢየሩሳሌም እስከ እልዋሪቆን ድረስ እየዞርኩ

ይህ ከኢየሩሳሌም ከተማ ከጣልያን ቅርብ ርቀት ላይ እስካለችው እስከ እልዋሪቆን ግዛት ድረስ ነው።