1016 B
1016 B
በእግዚአብሔር የተሰጠኝ ጸጋ
ጳውሎስ ጸጋን እግዚአብሔር በአካል እንደሰጠው የሚዳሰስ ስጦታ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል። ጳውሎስ ኢየሱስን ለመከተል ከመወሰኑ በፊት ብዙ አማኞችን ያሰቃየ ቢሆንም እግዚአብሔር ሐዋርያ እንዲሆን ሹሞታል። ይህን በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መተርጎም ትችላለህ። (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)
የአሕዛብ መስዋዕት ተቀባይ ይሆን ዘንድ
ጳውሎስ ወንጌል የመስበክ ስራውን ልክ እርሱ ካህን እንደሆነና ለእግዚአብሔር መስዋዕትን እንደሚያቀርብ አድርጎ ይስለዋል። አማራጭ ትርጉም፡- “አሕዛብ እግዚአብሔርን ሲታዝዙ እርሱን እንዲያስደስቱት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)