am_tn/rom/15/14.md

1.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፦

ጳውሎስ በሮም ያሉ አማኞች እግዚአብሔር እርሱን አሕዛብን ለመድረስ እንደመረጠው ያስታውሳቸዋል።

እኔ ራሴ ወንድሞቼ ሆይ … ስለ እናንተ ተረድቻለሁ

ጳውሎስ በሮም ያሉት አማኞች አንዱ ሌላውን በመልካም ባሕሪያቸው እያከበሩ እንደሆነ አርግጠኛ ነው። አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ራሴ እናንተ በሌሎች ዘንድ በመልካም አካሄድ እንደሄዳችሁ እርግጠኛ ነኝ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ወንድሞች

ይህ ማለት ሌሎች አማኞችን ያመለክታል፣ ወንዶችና ሴቶችንም ያካትታል።

በእውቀት ተሞልታችሁ

ጳውሎስ እዚህ ላይ ለንግግሩ አጽንዖት ለመስጠት ግነትን ይጠቀማል። አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔርን ለመከተል በሚበቃ እውቀት ተሞልታችሁ” (ግነት እና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እርስ በርሳችሁም ልትመካከሩ መቻላችሁ

እዚህ ላይ “ልትመካከሩ” የሚለው ማስተማርን ይወክላል። አማራጭ ትርጉም፡- “እርስ በርስ አንዱ ሌላውን ማስተማር መቻላችሁ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)