am_tn/rom/15/08.md

2.2 KiB

እላለሁ

ይህ ጳውሎስን ይወክላል (“እኔ” የሚለው አመልካች ጳውሎስን ይወክላል)

ክርስቶስ የመገረዝ አገልጋይ ሆኗል

እዚህ ላይ “መገረዝ” የሚለው አይሁድን የሚወክል ምትክ ስም ነው። ይህን በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መተርጎም ትችላለህ። አማራጭ ትርጉም፡- “ኢየሱስ ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ ሆነ” (ምትክ ስም እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የተስፋ ቃሉን ያጸና ዘንድ …. አሕዛብም እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ እንዲያከብሩት

እነዚህ ክርስቶስ የመገረዝ አገልጋይ የሆነበት ሁለት ዓላማዎች ወይም ምክንያቶች ናቸው። አማራጭ ትርጉም፡- “የተስፋ ቃሉን ያረጋግጥ ዘንድ … አሕዛብም ስለ ምሕረቱ እግዚአብሔርን እንዲያከብሩት”

ለአባቶች የሰጠውን የተስፋ ቃል

እዚህ ላይ “አባቶች” የሚለው የአይሑድ ሕዝቦችን አባቶች ያመለክታል። ይህንን በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መተርጎም ትችላለህ። አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ለአይሁድ ሕዝቦች አባቶች የሰጠውን የተስፋ ቃል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ተብሎ እንደተጻፈ

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መተርጎም ትችላለህ። አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ብሎ እንደጻፈው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ለስምህም ምስጋናን እዘምራለሁ

እዚህ ላይ “ለስምህ” የሚለው እግዚአብሔርን የሚወክል ምትክ ስም ነው። አማራጭ ትርጉም፡- “ለአንተ ምስጋናን እዘምራለሁ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)