am_tn/rom/15/03.md

2.1 KiB

ተብሎ እንደተጻፈው

እዚህ ላይ ጳውሎስ፣ ክርስቶስ (መሲሑ) ለእግዚአብሔር የሚናገርበትን አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ያነሳል። ይህን በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መተርጎም ትችላለህ። አማራጭ ትርጉም፡- “በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መሲሑ ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናግሯል …” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተን የሰደቡህ ሰዎች ስድብ እኔ ላይ ወደቀብኝ

እግዚአብሔርን የሰደቡት ሰዎች ስድብ በክርስቶስ ላይ ወደቀ።

አስቀድሞ የተጻፈው በሙሉ ለእኛ ትምህርት ተጽፏልና

ይህን በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መተርጎም ትችላለህ። አማራጭ ትርጉም፡- “ባለፉት ጊዜያት፣ ነቢያት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የጻፉት ሁሉም ነገር እኛን ለማስተማር የተጻፈ ነውና” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የኛ… እኛ

ጳውሎስ አንባቢዎቹንና ሌሎች አማኞችን ያካትታል። (አካታች “እኛ” የሚለውን ይመልከቱ)

ቃሉ በሚሰጠን ትዕግስትና ማበረታታት ተስፋ እንዲኖረን

እዚህ ላይ “ተስፋ እንዲኖረን” የሚለው አማኞች እግዚአብሔር የገባውን ቃል እንደሚፈጽም ማወቃቸውን ያመለክታል። የዚህን ትርጉም በትርጉምህ ውስጥ በግልጽ ማስቀመጥ ትችላለህ። አማራጭ ትርጉም፡- “በዚህ መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር የገባውን ቃል በሙሉ እንደሚያደርግልን እያወቅን በተስፋ እንድንጠባበቅ ያበረታናል።” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)