am_tn/rom/14/20.md

2.1 KiB

ለመብል ብለህ የእግዚአብሔርን ሥራ አታፍርስ

የዚህን አርፍተ ነገር ትርጉም ግልጽ አድርጎ መጻፍ ይቻላል። አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ የሆነ የምግብ ዓይነት መብላት ስለፈለግህ ብቻ እግዚአብሔር ለአንድ አማኝ የሰራውን ስራ አታፍርሰው” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን ለሚበላና ሌላው እንዲሰናከል ለሚያደርግ ለዚያ ሰው ክፉ ነው

እዚህ ላይ “ሌላውን እንዲሰናከል የሚያደርግ” ማለት ደካማ የሆነው ወንድም ከሕሊናው ጋር የማይጣጣም ነገር እንዲያደርግ የሚገፋው ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን አንድ ወንድም ሌላው ወንድም መብላት ትክክል አይደለም ብሎ የሚያስበውን ምግብ ቢበላ፣ ለዚያ ሰው ኃጢአት ይሆንበታል፣ እርሱ በመብላቱ ምክንያት ደካማውን ወንድም ከሕሊናው ጋር የማይጣጣም ነገር እንዲያደርግ ምክንያት ከሆነበት ኃጢአት ይሆንበታል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ስጋ መብላት፣ ወይንንም አለመጠጣት፣ እንደዚሁም ወንድምህን ያሰናክላል ብለህ የምታስበውን ነገር አለማድረግ መልካም ነው

“ስጋ መብላት፣ ወይን መጠጣት እንዲሁም ወንድምህ ኃጢአት እንዲያደርግ ምክንያት የሚሆን ነገርን አለማድረግ ይመረጣል”

ወንድም

ይህ ሌሎች አማኝ ክርስቲያኖችን ይወክላል፣ ወንድ ወይም ሴት ሊሆኑ ይችላሉ

የአንተ

“የአንተ” የሚለው በእምነቱ ጠንካራ የሆነውን ይወክላል፣ “ወንድም” የሚለው ደግሞ በእምነቱ ደካማ የሆነውን ይወክላል።