am_tn/rom/14/16.md

1.3 KiB

ስለዚህ አንተ መልካም ብለህ የቆጠርከውን ነገር ክፉ እንደሆነ ተደርጎ እንዲነገር አትፍቀድ

“ሌላ ሰው አንድ ነገር ክፉ ነው ብሎ ካሰበ፣ ያንን ነገር አንተ አታድርገው፣ ምንም እንኳ አንተ መልካም ነው ብለህ የምታስብ ቢሆንም አታድርገው”

የእግዚአብሔር መንግስት ጽድቅ፣ ሰላምና በመንፈስ ቅዱስ የሚሆን ደስታ እንጂ ምግብና መጠጥ አይደለምና

ጳውሎስ እግዚአብሔር መንግስቱን ያዘጋጀው ከራሱ ጋር ትክክለኛ የሆነ ግንኙነት እንዲኖረን ለማድረግ፣ እንዲሁም ሰላምንና ደስታን ሊሰጠን እንደሆነ በመናገር ይሞግታቸዋል። አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር መንግስቱን ያዘጋጀው የምንበላውንና የምንጠጣውን ለማስተዳደር አይደለም። መንግስቱን ያዘጋጀው ከእርሱ ጋር ትክክለኛ ግንኙነት እንዲኖረን፣ እንዲሁም ሰላምና ደስታን ሊሰጠን ነው። (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)