am_tn/rom/14/14.md

2.4 KiB

… ክርስቶስ ኢየሱስን አውቄያለሁ አምኛለሁም

እዚህ ላይ “አውቄያለሁ” እና “አምኛለሁ” የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉምን የያዙ ናቸው፡ ጳውሎስ እርግጠኛ መሆኑን አጽንኦት ለመስጠት ይጠቀምባቸዋል። አማራጭ ትርጉም፡- “ከጌታ ኢየሱስ ጋር ባለኝ ግንኙነት ምክንያት እርግጠኛ ነኝ” (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ምንም ነገር በራሱ ርኩስ አይደለም

ይህን በአዎንታዊ መልኩ መተርጎም ይቻላል። አማራጭ ትርጉም፡- “ሁሉም ነገር በራሱ ንጹህ ነው” (መንትያ አሉታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

በራሱ

“በተፈጥሮው” ወይም “በይዘቱ”

ምንም ነገር ርኩስ ነው ብሎ ለሚያስብ ፣ ለእርሱ ርኩስ ነው

ጳውሎስ እዚህ ላይ ለመናገር የፈለገው አንድ ሰው ርኩስ ነው ብሎ ከሚያስበው ነገር መራቅ እንዳለበት ነው። ይህን በትርጉምህ ግልጽ አድርገህ ማስቀመጥ ትችላለህ። አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን አንድ ሰው አንድን ነገር ርኩስ ነው ብሎ የሚያስብ ከሆነ፣ ለዚያ ሰው ያ ነገር ርኩስ ነውና ከእርሱ ሊርቅ ይገባዋል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በመብልህ ምክንያት ወንድምህ ቢጎዳ

“የሌላውን ክርስቲያን እምነት በመብል ምክንያት የምትጎዳ ከሆነ” እዚህ ላይ “በመብልህ” ውስጥ ያለው የባለቤት አመልካች የሚያመለክተው በእምነቱ ጠንካራ የሆነን አማኝ ነው፣ “ወንድም” የሚለው ደግሞ በእምነታቸው ደካማ የሆኑትን ያመለክታል።

ወንድም

ይህ ሌሎች ክርስቲያኖችን ይወክላል፣ ወንዶችንም ሴቶችንም ይወክላል

እንግዲያው በፍቅር እየተመላለስክ አይደለም

ጳውሎስ የአማኞችን ባሕርይ ጉዞ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል። አማራጭ ትርጉም፡- “ከእንግዲህ ፍቅርን እያሳየህ አይደለም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)