am_tn/rom/14/10.md

2.4 KiB

አንተ በወንድምህ ላይ ለምን ትፈርዳለህ? አንተስ ወንድምህን ለምን ትንቃለህ?

እነዚህን ጥያቄዎች በመጠቀም ጳውሎስ ከአንባቢዎቹ ውስጥ አንዳንድ ግለሰቦችን መገሰጽ እንደሚገባው ያሳያል። አማራጭ ትርጉም፡- “በወንድምህ ላይ መፍረድህ ትክክል አይደለም፣ ወንድምህንም መናቅ ትክክል አይደለም” ወይም “በወንድምህ ላይ መፍረድ፣ ወንድምህንም መናቅ አቁም!” (የሁለተኛ መደብ ቅርጾች የሚለውን ይመልከቱ)

ወንድም

ይህ ሌላ ክርስቲያን፣ ሴት ወይም ወንድ የሆነን ይወክላል።

ሁላችን በእግዚአብሔር የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለንና

“የፍርድ ዙፋን” የእግዚአብሔርን የመፍረድ ስልጣንን ያመለክታል። አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር በሁላችን ላይ ይፈርዳልና” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

…” ተብሎ ተጽፏልና

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ጽፎ ነበርና’ … ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ሕያው ነኝና

ይህ ሐረግ አንድን መሃላ ወይም ቃልኪዳንን ለመጀመር ጥቅም ላይ ይውላል። አማራጭ ትርጉም፡- “ይህ እውነት እንደሆነ እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእኔ ሁሉም ጉልበት ይንበረከካል፣ ሁሉም ምላስ ለእግዚአብሔር ምስጋናን ይሰጣል

ጳውሎስ “ጉልበት” እና “ምላስ” የመሳሰሉትን ቃላት የሚጠቀመው የአንድን ሰው ሙሉ ማንነት ለመወከል ነው። በተጨማሪም ጌታ “እግዚአብሔር” የሚለውን ቃል ራሱን ለመወከል ይጠቀማል። አማራጭ ትርጉም፡- “ሁሉም ሰው ይሰግዳል፣ ምስጋናንም ለእኔ ይሰጣል” (ወካይ እና አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)