am_tn/rom/14/07.md

983 B

ከእኛ ውስጥ ማንም ለራሱ የሚኖር የለም

እዚህ ላይ “ለራሱ የሚኖር” ማለት ራሱን ለማስደሰት ብቻ የሚኖር ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፡- “ማናችንም ራሳችንን ለማስደሰት ብቻ ብለን መኖር የለብንም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለራሱ የሚሞት ማንም የለም

ይህ ማለት የአንድ ሰው ሞት ሌሎች ሰዎችንም ይነካል ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፡- “ማናችንም እኛ ብቻ ስንሞት እኛን ብቻ እንደሚጎዳ ማሰብ የለብንም። (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እኛ … እኛ

ጳውሎስ አንባቢዎቹንም በዚህ ንግግር ውስጥ እያካተተ ነው። (አካታች “እኛ” የሚለውን ይመልከቱ)