am_tn/rom/14/05.md

2.4 KiB

አንድ ሰው አንድን ቀን ከሌላው ቀን አብልጦ ዋጋ ይሰጣል። ሌላው ግን ለሁሉም ቀኖች እኩል ዋጋ ይሰጣል

“አንድ ሰው አንድ ቀን ከሌላው ቀን የበለጠ እንደሆነ ያስባል፣ ሌላው ግን ሁሉም ቀናት እኩል እንደሆኑ ያስባል።

እያንዳንዱ ሰው በራሱ አእምሮ የሚያስበውን ይመን

የዚህን ትርጉም በግልጽ መናገር ይቻላል። ይህንን በገቢር/አድራጊ ቅርጽም መጻፍ ይቻላል። አማራጭ ትርጉም፡- “እያንዳንዱ ሰው የሚያደርገው ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንደሆነ እርግጠኛ ይሁን” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ቀንን የሚያከብር፣ ለጌታ ብሎ ያከብራል

እዚህ ላይ “ማክበር” የሚለው ማምለክን ያመለክታል። አማራጭ ትርጉም፡- “በአንድ በተወሰነ ቀን የሚያመልክ ሰው ይህን የሚያደርገው እግዚአብሔርን ለማክበር ነው” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የሚበላ

“ሁሉንም” የሚለው ቃል ሮሜ 14:03 ላይ ባለው አገባብ መረዳት ይቻላል። እዚህ ላይ ተደግሞ ሊጻፍ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “ሁሉንም አይነት ምግብ የሚበላ ሰው” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

ለጌታ ብሎ ይበላል

“እግዚአብሔርን ለማክበር ይበላል” ወይም “በዚያ መንገድ የሚበላው እግዚአብሔርን ለማክበር ነው”

የማይበላ

“ሁሉንም” የሚለው ቃል በሮሜ ሮሜ 14:03 ላይ ባለው አገባብ መሰረት መረዳት ይቻላል። እዚህ ላይ ተደግሞ ሊጻፍ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “ሁሉንም የማይበላ” ወይም “አንዳንድ የምግብ ዓይነቶችን የማይበላ ሰው” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

ለጌታ ብሎ ከመብላት ይቆጠባል

“እነዚያን የምግብ ዓይነቶች ጌታን ለማክበር ሲል ከመብላት ይቆጠባል” ወይም “በዚያ መንገድ የሚበላው ጌታን ለማክበር ነው”